ለሴሰኞች፥ ከወንድ ጋርም ለሚተኙ፥ በሰዎችም ለሚነግዱ፥ ለሐሰተኞችም፥ በውሸትም ለሚምሉና የእውነተኛ ትምህርት ተቃራኒ የሆነውን ነገር ሁሉ ለሚያደርጉ ነው።
ቲቶ 2:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንተ ግን ከእውነተኛ አስተምሮ ጋር የሚጣጣመውን ነገር አስተምር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንተ ግን ከትክክለኛው ትምህርት ጋራ ተስማሚ የሆነውን አስተምር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንተ ግን ሕይወት የሚገኝበትን ትምህርት አስተምር፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተ ግን ሕይወት ለሚገኝበት ትምህርት የሚገባውን ተናገር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንተ ግን ሕይወት ለሚገኝበት ትምህርት የሚገባውን ተናገር። |
ለሴሰኞች፥ ከወንድ ጋርም ለሚተኙ፥ በሰዎችም ለሚነግዱ፥ ለሐሰተኞችም፥ በውሸትም ለሚምሉና የእውነተኛ ትምህርት ተቃራኒ የሆነውን ነገር ሁሉ ለሚያደርጉ ነው።
ማንም ሰው ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ከታመኑ ቃላት ጋራ የማይስማማና እግዚአብሔርን በመምሰል ላይ መሠረት ካደረገው ትምህርት ጋር የማይጣጣም ልዩ ትምህርት የሚያስተምር ከሆነ፥
ቃሉ የታመነ ነው። እግዚአብሔርንም የሚያምኑት በመልካም ሥራ በጥንቃቄ እንዲተጉ፥ እነዚህን አስረግጠህ እንድትናገር እፈቅዳለሁ። ይህ መልካምና ለሰዎች የሚጠቅም ነው፤
ማንም ሰው የሚናገር ቢሆን፥ እንደ እግዚአብሔር ቃል ይናገር፤ የሚያገለግልም ቢሆን፥ እግዚአብሔር በሚሰጠው ኃይል ያገልግል፤ በዚህም ዓይነት በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብራል፤ ክብርና ሥልጣን ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ለእርሱ ይሁን፤ አሜን።