ለባርያህ ካሳየኸው ከጽኑ ፍቅርና ከታማኝነትህ ሁሉ ትንሽ ስንኳ የማይገባኝ ነኝ፥ በትሬን ብቻ ይዤ ይህን ዮርዳኖስን ተሻግሬ ነበር፥ አሁን ግን ለሁለት ወገን የተከፈልኩ ሆንሁ።
ማሕልየ መሓልይ 4:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከንፈሮችሽ እንደ ቀይ ሐር ፈትል ናቸው፥ አፍሽም ያማረ ነው፥ በመሸፈኛሽ ውስጥ ጉንጭና ጉንጭሽ እንደ ተከፈለ ሮማን ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከንፈሮችሽ ቀይ የሐር ፈትል ይመስላሉ፤ አፍሽም ውብ ነው፤ ከመሸፈኛሽ ውስጥ ያሉት ጕንጮችሽ፣ ለሁለት የተከፈለ ሮማን ይመስላሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከንፈሮችሽ እንደ ቀይ ሐር ፈትል ያማሩ ናቸው፤ ስትነጋገሪም እጅግ ደስ ያሰኛሉ፤ ሁለቱ ጒንጮችሽ በፊትሽ መሸፈኛ ዐይነ ርግብ ውስጥ ሲታዩ ለሁለት የተከፈለ የሮማን ፍንካች ይመስላሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከንፈሮችሽ እንደ ቀይ ሐር ፈትል ናቸው፥ ቃልሽም ያማረ ነው፤ ከዝምታሽ በቀር ጕንጮችሽ እንደ ተከፈለ ሮማን ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከንፈሮችሽ እንደ ቀይ ሐር ፈትል ናቸው፥ አፍሽም ያማረ ነው፥ በዓይነ ርግብ መሸፈኛሽ ውስጥ ጕንጭና ጕንጭሽ እንደ ተከፈለ ሮማን ናቸው። |
ለባርያህ ካሳየኸው ከጽኑ ፍቅርና ከታማኝነትህ ሁሉ ትንሽ ስንኳ የማይገባኝ ነኝ፥ በትሬን ብቻ ይዤ ይህን ዮርዳኖስን ተሻግሬ ነበር፥ አሁን ግን ለሁለት ወገን የተከፈልኩ ሆንሁ።
እንዲህም አልሁ፦ “አምላኬ ሆይ፥ አፍሬአለሁ፤ አምላኬ ሆይ፥ ፊቴንም ወደ አንተ ለማንሣት እፈራለሁ፥ ኃጢአታችን ከራሳችን በላይ ከፍ ብሏልና፥ በደላችንም ወደ ሰማያት ወጥቷልና።
ጉንጩና ጉንጩ የሽቱ መደብ እርከን እንዳለበት እንደ ሽቱ አትክልት ናቸው፥ ከንፈሮቹ እንደ አበቦች ናቸው፥ የሚፈስስ ከርቤንም ያንጠበጥባሉ።
ያደረግሽውን ሁሉ ይቅር ባልሁሽ ጊዜ፥ እንድታስቢውና እንድታፍሪ፥ ከውርደትሽም የተነሣ ደግሞ አፍሽን እንዳትከፍቺ ነው፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
በሕይወት ያለውን ወፍ፥ የዝግባውንም እንጨት፥ ቀዩንም ግምጃ፥ ሂሶጱንም ወስዶ ይነክራቸዋል፥ በሕይወትም ያለውን ወፍ በምንጭ ውኃ ላይ በታረደው የወፍ ደም ውስጥ ይዘፍቀዋል።
እያንዳንዱን የሕግ ትእዛዝ በሙሴ ለሕዝቡ ከተነገረ በኋላ የጥጆችን ደም ከውሃ፥ ከቀይ የበግ ጠጒርና ከሂሶጵ ጋር ወስዶ፥ በመጽሐፉና በሕዝቡ ላይ ረጨው፤
እነሆ፥ እኛ ወደ አገሩ በገባን ጊዜ ይህን ቀይ ፈትል እኛን ባወረድሽበት መስኮት በኩል እሰሪው፤ አባትሽንም እናትሽንም ወንድሞችሽንም የአባትሽንም ቤተሰብ ሁሉ ወደ አንቺ ወደ ቤትሽ ሰብስቢ።