ማሕልየ መሓልይ 2:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወይናችን አብቦአልና የወይናችንን ቦታ የሚያጠፉትን ቀበሮች፥ ትናንሾችን ቀበሮች አጥምዳችሁ ያዙልን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የወይን ተክሉን ቦታ፣ በማበብ ላይ ያለውን የወይን ተክል ቦታችንን፣ የሚያጠፉትን ቀበሮዎች፣ እነዚያን ትንንሽ ቀበሮዎች አጥምዳችሁ ያዙልን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወይናችን አብቦአል፤ ስለዚህ የወይን ተክላችንን እንዳያጠፉብን ቀበሮዎችን፥ እነኛን ትናንሽ ቀበሮዎችን አጥምዳችሁ ያዙልን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የወይን ቦታችን ያብብ ዘንድ፥ የወይናችንን ቦታ የሚያጠፉትን ጥቃቅኑን ቀበሮች አጥምዳችሁ ያዙልን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወይናችን አብቦአልና የወይናችንን ቦታ የሚያጠፉትን ቀበሮች፥ ጥቃቅኑን ቀበሮች አጥምዳችሁ ያዙልን። |
እንዲህም አላቸው “ሄዳችሁ ለዚያች ቀበሮ ‘እነሆ፥ ዛሬና ነገ አጋንንትን አወጣለሁ፤ በሽተኞችንም እፈውሳለሁ፤ በሦስተኛውም ቀን እፈጽማለሁ’ በሉአት።
“ሥራህንና ድካምህን ትዕግሥትህንም አውቃለሁ፤ ክፉዎችንም ልትታገሥ እንደማትችል፥ እንዲሁም ሐዋርያት ሳይሆኑ ‘ነን’ የሚሉትን መርምረህ ሐሰተኞች ሆነው እንዳገኘሃቸው አውቃለሁ፤