ከመሠዊያው ምድጃ አጠገብ ቆሞ፥ ከካህናቱ እጅ ድርሻዎቹን ሲቀበል፥ የሊባኖስ ዝግባ በቅጠሉ እንደሚሸፈን፥ በዘንባባ ግንዶች እንደተከበበ ሁሉ፥ እርሱንም ወንድሞቹ ከበውት አክሊል ይሆኑታል።
ከካህናቱም እጅ የመሥዋዕቱን ሥጋ ክፍል በተቀበለ ጊዜ፥ በመሠዊያው አጠገብ ይቆም ነበር፤ ወንድሞቹም በዙሪያው ቁመው ይጋርዱት ነበር፤ እንደ ሊባኖስ ለጋ ዝግባና እንደ ዘንባባም ዛፍ ይከቡት ነበር።