ሳትዘገይ ወደ እግዚአብሔር ተመለስ፤ ነገ ከነገ ወዲያ እያልህ ቀኑን አታራዝም፤ ምክንያቱም የእግዚአብሔር ቁጣ በድንገት ከተፍ ይላል፤ በቅጣት ቀን ትደመሰሳለህ።
ለእግዚአብሔር መገዛትን ቸል አትበል። ሞት ድንገት ትመጣለችና ከቀን ቀን አታሳልፍ፤ ፍዳህ ከመቅሠፍት ጋራ በመጣብህ ጊዜ በመከራ ትጨነቃለህ።