በጥበብ የሠራቸውን ድንቅ ሥራዎች አስውቧቸዋል፤ መጀመሪያም መጨረሻም የለውም፥ ምንም አይቀነስበትም፥ ምንም አይጨመርበትም፥ እርሱ የማንንም ምክር አይሻም።
የጥበቡን ገናናነት አስጌጠ። ይህቺም ዓለም ሳይፈጠር የነበረች ናት፥ ለዘለዓለሙም ትኖራለች፤ አትጨምርም፤ አትጐድልምም፤ አንድ መካርን ስንኳ አይፈልግም።