እርሱም ወደ ያቤሽ ገለዓድ መልእክተኞችን ልኮ እንዲህ አላቸው፥ “በእንዲህ ዓይነት ሁኔታ ጌታችሁን ሳኦልን በመቅበር በጎነት በማሳየታችሁ ጌታ ይባርካችሁ፤
ሩት 2:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ናዖሚም ምራትዋን፦ “በሕያዋን እና በሙታን ላይ ቸርነቱ የማያልቅበት ጌታ የተባረከ ይሁን” አለቻት። ናዖሚም ደግሞ፦ “ይህ ሰው የቅርብ ዘመዳችን ነው፥ እርሱም ሊቤዡን ከሚችሉት አንዱ ነው” አለቻት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኑኃሚንም ምራቷን፣ “በጎነቱን ለሕያዋንም ሆነ ለሙታን ማድረጉን ያልተወ እግዚአብሔር ይባርከው” አለቻት፤ ቀጥላም፣ “ሰውየው እኮ የሥጋ ዘመዳችን ነው፤ የመቤዠት ግዴታ ካለባቸው ዘመዶቻችን አንዱ እርሱ ነው” አለቻት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ናዖሚም “ለሕያዋንና ለሙታን የሰጠውን ተስፋ የሚፈጽም አምላክ ቦዔዝን ይባርከው!” አለች፤ ቀጥላም “ያ ሰው እኮ የቅርብ ዘመዳችን ነው! እንዲያውም ለእኛ ኑሮ የማሰብ ኀላፊነት ካለባቸው ሰዎች አንዱ እርሱ ነው” አለች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኑኃሚንም ምራትዋን፦ ቸርነቱን በሕያዋንና በሙታን ላይ አልተወምና በእግዚአብሔር የተባረከ ይሁን አለቻት። ኑኃሚንም ደግሞ፦ ይህ ሰው የቅርብ ዘመዳችን ነው፥ እርሱም ሊቤዡን ከሚችሉት አንዱ ነው አለቻት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኑኃሚንም ምራትዋን “ቸርነቱን በሕያዋንና በሙታን ላይ አልተወምና በእግዚአብሔር የተባረከ ይሁን፤” አለቻት። ኑኃሚንም ደግሞ “ይህ ሰው የቅርብ ዘመዳችን ነው፤ እርሱም ሊቤዡን ከሚችሉት አንዱ ነው፤” አለቻት። |
እርሱም ወደ ያቤሽ ገለዓድ መልእክተኞችን ልኮ እንዲህ አላቸው፥ “በእንዲህ ዓይነት ሁኔታ ጌታችሁን ሳኦልን በመቅበር በጎነት በማሳየታችሁ ጌታ ይባርካችሁ፤
ነገር ግን አሁን ከጊዜ በኋላ ስለ እኔ እንደገና ማሰብ ስለ ጀመራችሁ፥ በጌታ እጅግ ደስ ተሰኝቻለሁ፤ አጋጣሚዎች አልተመቻቹላችሁም እንጂ፥ ማሰብስ ታስቡ ነበር።
አንተም ስለዚህ ጉዳይ ማወቅ የሚገባህ ይመስለኛል፤ እንግዲህ መሬቱን ከፈለግኸው እዚህ በተቀመጡትና በሕዝቤ ሽማግሌዎች ፊት ለራስህ ልታስቀረው ትችላለህ፤ የማትፈልገው ከሆነ ግን ቁርጡን ንገረኝ፤ መሬቱን የማስቀረት ቅድሚያ ያለህ አንተ ነህ፤ ከአንተም ቀጥሎ እኔ ነኝ።” ሰውየውም “እኔም እቤዥዋለሁ” አለ።
የቅርብ ዘመዱም፦ “የራሴን ርስት እንዳላበላሽ መውሰድ አልችልም፥ እኔ የራሴ ላደርገው አልችልምና አንተ እንድትወስደው ፈቅጄልሃለሁ” አለው።