ሩት 2:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእርሻውም ውስጥ እስከ ማታ ድረስ ቃረመች፥ የቃረመችውንም ወቃችው፥ ዐሥር ኪሎ ያህልም ገብስ ሆነ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ሩት እስኪመሽ ድረስ ከአዝመራው ላይ ቃረመች፤ ከዚያም የሰበሰበችውን ገብስ ወቃች፤ አንድ የኢፍ መስፈሪያም ያህል ሆነ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሩትም እስከ ምሽት ድረስ ከእርሻው እህል ስትቃርም ዋለች፤ ባሸችውም ጊዜ ዐሥር ኪሎ ያኽል ሆነ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእርሻውም ውስጥ እስከ ማታ ድረስ ቃረመች፣ የቃረመችውንም ወቃችው፣ አንድ የኢፍ መስፈሪያ ያህልም ገብስ ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእርሻውም ውስጥ እስከ ማታ ድረስ ቃረመች፤ የቃረመችውንም ወቃችው፤ አንድ የኢፍ መስፈሪያ ያህልም ገብስ ሆነ። |