ሮሜ 9:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደግሞም፥ ‘እናንተ ሕዝቤ አይደላችሁም’ ተብሎ በተነገረላቸው ስፍራ፥ በዚያ ‘የሕያው እግዚአብሔር ልጆች’ ተብለው ይጠራሉ።” ይላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደግሞም፣ “ ‘ሕዝቤ አይደላችሁም’ ተብሎ በተነገራቸው በዚያ ቦታ፣ ‘የሕያው እግዚአብሔር ልጆች’ ተብለው ይጠራሉ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱ ‘ሕዝቤ አይደላችሁም’ በተባሉበት ስፍራ ‘የሕያው እግዚአብሔር ልጆች’ ተብለው ይጠራሉ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔር ወገኖች አይደላችሁም ይባሉ በነበሩበት ሀገርም የእግዚአብሔር ልጆች ይሆናሉ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተ ሕዝቤ አይደላችሁም በተባለላቸውም ስፍራ በዚያ የሕያው እግዚአብሔር ልጆች ተብለው ይጠራሉ ይላል። |