ሮሜ 7:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኃጢአት ግን በትእዛዝ አማካኝነት አጋጣሚን በመውሰድ ሁሉንም ዓይነት ምኞትን አስነሣ፤ ኃጢአት ያለ ሕግ የሞተ ነውና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኀጢአት ግን ትእዛዙ ባስገኘው ዕድል ተጠቅሞ በእኔ ውስጥ ማንኛውንም ዐይነት ዐጕል ምኞት አስነሣ፤ ኀጢአት ያለ ሕግ ምዉት ነውና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኃጢአት ከሕግ በመጣው ትእዛዝ ዕድል አግኝቶ ምኞትን ሁሉ በኔ ውስጥ እንዲቀሰቀስ አደረገ። ሕግ ከሌለ ግን ኃጢአት የሞተ ነገር ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያችም ትእዛዝ ለኀጢአት ምክንያት ሆነቻት፤ ምኞትንም ሁሉ አመጣችብኝ፤ ቀድሞ ግን ኦሪት ሳትሠራ ኀጢአት ሙት ነበረች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኃጢአት ግን ምክንያት አግኝቶ ምኞትን ሁሉ በትእዛዝ ሠራብኝ፤ ኃጢአት ያለ ሕግ ምውት ነውና። |
እንግዲህ መልካም የሆነው ነገር ሞት ሆነብኝን? በጭራሽ! ነገር ግን ኃጢአት ኃጢአትነቱ እንዲታይ፥ መልካም በሆነው ነገር ሞትን ይሠራብኝ ነበር። ይኸውም ኃጢአት በትእዛዝ አማካይነት ያለ ልክ ኃጢአት እንዲሆን ነው።