ሮሜ 5:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስጦታውም አንድ ሰው ኃጢአትን በማድረጉ እንዳመጣው ውጤት አይደለም፤ በአንድ በኩል፥ ፍርዱ የአንድን ሰው በደል ተከትሎ ኩነኔን አመጣ፤ በሌላ በኩል ግን ስጦታው ብዙ በደልን ተከትሎ ጽድቅን አመጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደግሞም የእግዚአብሔር ስጦታ እንደ አንዱ ሰው የኀጢአት ውጤት አይደለም፤ ምክንያቱም ፍርዱ የአንድን ሰው ኀጢአት ተከትሎ ኵነኔን አመጣ፤ ስጦታው ግን አያሌ መተላለፍን ተከትሎ ጽድቅን አመጣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም የእግዚአብሔር ነጻ ስጦታው ያመጣው ጸጋ ውጤት የአንድ ሰው ኃጢአት እንዳመጣው ውጤት አይደለም። በአንድ ሰው ኃጢአት ምክንያት የተሰጠው ፍርድ ቅጣትን አመጣ፤ በብዙ ኃጢአት ምክንያት የተሰጠው ነጻ ስጦታ ጽድቅን አመጣ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔር ጸጋው በአንዱ ሰው ኀጢአት መጠን የሆነብን አይደለም፤ የኀጢአት ፍርድ ከአንድ ሰው ወጥታ ሁሉ ከተቀጣባት፥ ጸጋው ከበደላችን እንደ ምን ያነጻን ይሆን? የዘለዓለምንስ ሕይወት እንዴት ይሰጠን ይሆን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንድ ሰውም ኃጢአትን በማድረጉ እንደ ሆነው መጠን እንደዚያው ስጦታው አይደለም፤ ፍርድ ከአንድ ሰው ለኵነኔ መጥቶአልና፥ ስጦታው ግን በብዙ በደል ለማጽደቅ መጣ። |
ከሕግ ሥራ የሆኑት ሁሉ ከርግማን በታች ናቸው፤ “በሕግ መጽሐፍ በተጻፉት ሁሉ የማይኖርና የማይፈጽማቸው ሁሉ የተረገመ ይሁን፤” ተብሎ ተጽፎአልና።