Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሮሜ 5:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋው በአ​ንዱ ሰው ኀጢ​አት መጠን የሆ​ነ​ብን አይ​ደ​ለም፤ የኀ​ጢ​አት ፍርድ ከአ​ንድ ሰው ወጥታ ሁሉ ከተ​ቀ​ጣ​ባት፥ ጸጋው ከበ​ደ​ላ​ችን እንደ ምን ያነ​ጻን ይሆን? የዘ​ለ​ዓ​ለ​ም​ንስ ሕይ​ወት እን​ዴት ይሰ​ጠን ይሆን?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ደግሞም የእግዚአብሔር ስጦታ እንደ አንዱ ሰው የኀጢአት ውጤት አይደለም፤ ምክንያቱም ፍርዱ የአንድን ሰው ኀጢአት ተከትሎ ኵነኔን አመጣ፤ ስጦታው ግን አያሌ መተላለፍን ተከትሎ ጽድቅን አመጣ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ስጦታውም አንድ ሰው ኃጢአትን በማድረጉ እንዳመጣው ውጤት አይደለም፤ በአንድ በኩል፥ ፍርዱ የአንድን ሰው በደል ተከትሎ ኩነኔን አመጣ፤ በሌላ በኩል ግን ስጦታው ብዙ በደልን ተከትሎ ጽድቅን አመጣ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 እንዲሁም የእግዚአብሔር ነጻ ስጦታው ያመጣው ጸጋ ውጤት የአንድ ሰው ኃጢአት እንዳመጣው ውጤት አይደለም። በአንድ ሰው ኃጢአት ምክንያት የተሰጠው ፍርድ ቅጣትን አመጣ፤ በብዙ ኃጢአት ምክንያት የተሰጠው ነጻ ስጦታ ጽድቅን አመጣ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 አንድ ሰውም ኃጢአትን በማድረጉ እንደ ሆነው መጠን እንደዚያው ስጦታው አይደለም፤ ፍርድ ከአንድ ሰው ለኵነኔ መጥቶአልና፥ ስጦታው ግን በብዙ በደል ለማጽደቅ መጣ።

Ver Capítulo Copiar




ሮሜ 5:16
14 Referencias Cruzadas  

“ኑና እን​ዋ​ቀስ” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ኀጢ​አ​ታ​ችሁ እንደ አለላ ቢሆን እንደ በረዶ አነ​ጻ​ዋ​ለሁ፤ እንደ ደምም ቢቀላ እንደ ባዘቶ አጠ​ራ​ዋ​ለሁ።


መተ​ላ​ለ​ፍን፦ ስለ እኔ ስለ ራሴ ስል የም​ደ​መ​ስስ እኔ ነኝ፤ ኀጢ​አ​ት​ህ​ንም አላ​ስ​ብም።


መተ​ላ​ለ​ፍ​ህን እንደ ደመና፥ ኀጢ​አ​ት​ህ​ንም እንደ ጭጋግ ደም​ስ​ሼ​አ​ለሁ፤ ተቤ​ዥ​ች​ሃ​ለ​ሁና ወደ እኔ ተመ​ለስ።


ለሚ​ቃ​ጠ​ልም መሥ​ዋ​ዕት ከመ​ን​ጋ​ዎች አንድ ወይ​ፈን፥ አንድ አውራ በግ፥ አንድ የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦት፤


ለሰዎች ኀጢአታቸውን ይቅር ብትሉ፥ የሰማዩ አባታችሁ እናንተን ደግሞ ይቅር ይላችኋልና፤


እን​ግ​ዲህ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ላሉት በመ​ን​ፈስ እንጂ በሥጋ ለማ​ይ​መ​ላ​ለሱ ፍርድ የለ​ባ​ቸ​ውም።


ነገር ግን በተ​ፈ​ረ​ደ​ብን ጊዜ ከዓ​ለም ጋር እን​ዳ​ን​ኰ​ነን በጌታ እን​ገ​ሠ​ጻ​ለን።


በኦ​ሪት ሕግ ያሉ ሁሉ በእ​ር​ግ​ማን ውስጥ ይኖ​ራሉ፤ መጽ​ሐፍ እን​ዲህ ብሎ​አ​ልና፥ “በዚህ በኦ​ሪት መጽ​ሐፍ ውስጥ የተ​ጻ​ፈ​ውን ሁሉ የማ​ይ​ፈ​ጽ​ምና የማ​ይ​ጠ​ብቅ ርጉም ይሁን።”


ሕግን ሁሉ የሚጠብቅ፥ ነገር ግን በአንዱ የሚሰናከል ማንም ቢኖር በሁሉ በደለኛ ይሆናል፤ “አታመንዝር” ያለው ደግሞ “አትግደል” ብሎአልና፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos