ሮሜ 3:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን የእግዚአብሔር እውነተኛነት በእኔ ውሸት ለክብሩ ከሞላ፥ ለምን እኔ እስካሁን እንደ ኃጢአተኛ ይፈረድብኛል? አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የእኔ ውሸተኛ መሆን የእግዚአብሔርን እውነተኛነት የሚያጐላ፣ ክብሩንም የሚጨምርለት ከሆነ፣ ኀጢአተኛ ተብዬ እስካሁን እንዴት ይፈረድብኛል?” በማለት ሊከራከር የሚችል ሰው ይኖር ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን የእኔ ሐሰተኛነት የእግዚአብሔርን እውነት በመግለጥ፥ የክብሩን ብዛት የሚያሳይ ከሆነ ታዲያ፥ እኔ እንደ ኃጢአተኛ የሚፈረድብኝ ስለ ምንድን ነው? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔር እውነት በእኔ ሐሰተናነት ለክብሩ ከፍ ከአለ እንግዲህ እኔን እንደ ኀጢአተና ለምን ይፈርድብናል? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእኔ ውሸት ግን የእግዚአብሔር እውነት ለክብሩ ከላቀ ስለምን በእኔ ደግሞ እንደ ኃጢአተኛ ገና ይፈርድብኛል? |
ሕዝቡም ማምለጣቸውን ለግብጽ ንጉሥ ነገሩት፤ የፈርዖንና የአገልጋዮቹም ልብ በሕዝቡ ላይ ተለወጠና፦ “ምንድነው ያደረግነው? እንዳያገለግለን እስራኤልን ለቀቅነው” አሉ።
በጭራሽ! “በቃልህ እውነተኛ እንድትሆን፥ ለፍርድ በቀረብክም ጊዜ አሸናፊ እንድትሆን፤” ተብሎ እንደ ተጻፈ፤ ሰው ሁሉ ሐሰተኛ ቢሆንም፥ እግዚአብሔር ግን እውነተኛ ይሁን።