Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሮሜ 3:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 “መልካም ነገር እንዲመጣ ለምን ክፉ አናደርግም?” ይላሉ ብለው እንደሚያሙን አይደለም፤ የሚፈረድባቸው ፍርድ ትክክለኛ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ይህማ “በጎ እንዲመጣ ክፉ እንሥራ” ይላሉ በማለት አንዳንዶች እንደሚያስወሩብን ነው፤ በእነዚህ ሰዎች ላይ የሚደርሰው ፍርድ ትክክለኛ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 አንዳንድ ሰዎች “መልካም ነገር እንድናገኝ ክፉ ነገር እናድርግ” እያልኩ የማስተምር አስመስለው ይከሱኛል፤ ስለዚህ እንዲህ ባሉት ላይ የሚፈረድባቸው ፍርድ ትክክለኛ ነው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 በውኑ እና መል​ካም ነገር እና​ገኝ ዘንድ ክፉ ነገር እና​ድ​ርግ እን​ደ​ም​ንል አስ​መ​ስ​ለው የሚ​ጠ​ረ​ጥ​ሩ​ንና የሚ​ነ​ቅ​ፉን ሰዎች እን​ደ​ሚ​ሰ​ድ​ቡን ነን? ለእ​ነ​ር​ሱስ ቅጣ​ታ​ቸው ተዘ​ጋ​ጅ​ቶ​ላ​ቸ​ዋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ስለ ምንስ መልካም እንዲመጣ ክፉ አናደርግም? እንዲሁ ይሰድቡናልና አንዳንዱም እንዲሁ እንድንል ይናገራሉና። የእነርሱም ፍርድ ቅን ነው።

Ver Capítulo Copiar




ሮሜ 3:8
10 Referencias Cruzadas  

የአኪቃም ልጅ ጎዶልያስ ግን የቃሬያን ልጅ ዮሐናንን፦ “በእስማኤል ላይ ሐሰት ተናግረሃልና ይህን ነገር አታድርግ” አለው።


“ሲሰድቡአችሁና ሲያሳድዱአችሁ በእኔም ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብፁዓን ናችሁ።


በደል እንዲበዛ ሕግ ገባ፤ ነገር ግን ኃጢአት በበዛበት፥ ጸጋ ይበልጥ በዛ፤


እንግዲህ ምን እንላለን? ጸጋ እንዲበዛ ኃጢአት በመሥራት እንቀጥል?


እንግዲህ ምን ይሁን? ከሕግ በታች ሳይሆን ከጸጋ በታች ስለ ሆንን ኃጢአት መሥራት አለብንን? በጭራሽ!


እንግዲህ ምን እንላለን? ሕግ ኃጢአት ነውን? በጭራሽ! ነገር ግን በሕግ በኩል ባይሆን ኖሮ ኃጢአትን አላውቅም ነበር፤ ሕጉ “አትመኝ” ባይል ኖሮ ምኞትን አላውቅም ነበር።


እንግዲህ አገልጋዮቹ ደግሞ የጽድቅን አገልጋዮች በመምሰል ራሳቸውን ቢለዋውጡ እንግዳ ነገር አይደለም፤ ፍጻሜአቸውም እንደ ሥራቸው ይሆናል።


በክብርና በውርደት፥ በመመስገንና በመሰደብ ኖረናል። አሳቾች ስንባል እውነተኞች ነን፤


አስቀድሞ ለዚህ ፍርድ የተጻፉ አንዳንዶች ሰዎች ሾልከው ገብተዋልና፤ ኃጢአተኞች ሆነው የአምላካችንን ጸጋ በዝሙት ይለውጣሉ፤ ብቸኛ ንጉሣችንና ጌታችን የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን ይክዳሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos