“አፋቸውም እርግማንና መራርነት ሞልቷል፤”
“አፋቸው ርግማንና ምሬት ሞልቶበታል።”
አፋቸውም እርግማንና መራርነት ሞልቶበታል።
አፋቸው መራራ ነው፤ መርገምንም የተሞላ ነው።
አፋቸውም እርግማንና መራርነት ሞልቶበታል፤
አፉ በመርገም፥ በሽንገላና በዐመፃ የተመላ ነው፥ ከምላሱ በታች ተንኰልና ክፋት አሉ።
ሕግህን እንዳይረሱ አትግደላቸው፥ አቤቱ ጋሻዬ፥ በኃይልህ በትናቸው አውርዳቸውም።
መራርነትና ንዴት ቁጣም፥ ጩኸትና ስድብን ሁሉ፥ ከክፋት ሁሉ ጋር ከእናንተ ዘንድ ይወገድ።
ከአንድ አፍ በረከትና መርገም ይወጣሉ፤ ወንድሞቼ ሆይ! ይህ ሊሆን አይገባም።