ሮሜ 16:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መታዘዛችሁ በሁሉም ሰው ዘንድ ደርሶአልና፤ እንግዲህ በእናንተ ደስ ይለኛል፤ ነገር ግን ለመልካም ነገር ጥበበኞች ለክፉ ነገር የዋሆች እንድትሆኑ እፈልጋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእናንተን ታዛዥነት ሁሉም ሰምተዋል፤ በዚህም እኔ እጅግ ተደስቻለሁ። ሆኖም በጎ ስለ ሆነው ነገር ጥበበኞች፣ ክፉ ስለ ሆነውም የዋሆች እንድትሆኑ እፈልጋለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለወንጌል ቃል ታዛዦች መሆናችሁ በሰው ሁሉ ዘንድ ስለ ታወቀ ደስ ያለኝ ቢሆንም፥ ነገር ግን ለመልካም ነገር ጥበበኞች ለክፉ ነገር ግን የዋሆች እንድትሆኑ እፈልጋለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መታዘዛችሁም በሁሉ ዘንድ ተሰምቶአል፤ እኔም በእናንተ ደስ ይለናል፤ ለመልካም ነገር ጠቢባን፥ ለክፉ ነገርም የዋሃን እንድትሆኑ እፈልጋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መታዘዛችሁ ለሁሉ ተወርቶአልና፤ እንግዲህ በእናንተ ደስ ይለኛል፤ ነገር ግን ለበጎ ነገር ጥበበኞች ለክፉም የዋሆች እንድትሆኑ እወዳለሁ። |
“ሕዝቤ ሰንፈዋልና አላወቁኝም፤ ሰነፎች ልጆች ናቸው፥ ማስተዋልም የላቸውም፤ ክፉ ነገርን ለማድረግ ብልሃተኞች ናቸው፥ በጎ ነገርን ማድረግ ግን አያውቁም።”
በዚህም በመጥፎና በጠማማ ትውልድ መካከል ሆናችሁ በዚህ ዓለም እንደ ከዋክብት የምታበሩ፥ ያለ ነቀፋ የዋሆችና ነውርም የሌለባችሁ የእግዚአብሔር ልጆች ትሆናላችሁ፤
የክርስቶስ ቃል በሙላት በእናንተ ይኑር፤ በጥበብ ሁሉ እርስ በርሳችሁ ተማማሩ፤ ተመካከሩም፤ በመዝሙርና በውዳሴ በመንፈሳዊም ዝማሬ በልባችሁ በማመስገን ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤