ይህም በተፈጸመ ጊዜ ጳውሎስ “ወደዚያ ደርሼ ሮሜን ደግሞ አይ ዘንድ ይገባኛል፤” ብሎ በመቄዶንያና በአካይያ አልፎ ወደ ኢየሩሳሌም እንዲሄድ በመንፈስ አሰበ።
ሮሜ 15:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሁን ግን በዚህ አገር ስፍራ ከእንግዲህ ወዲያ የለኝም፥ ከብዙ ዓመታት ጀምሮም ወደ እናንተ ልመጣ ናፍቆት ስላለኝ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሁን ግን በእነዚህ አካባቢዎች የምሠራው ስለሌለ፣ ከብዙ ዓመታት ጀምሮ እናንተን ለማየት እናፍቅም ስለ ነበር፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሁን ግን በዚህ አካባቢ ባሉት አገሮች የምሠራባቸው ቦታዎች ስለሌሉ፥ እንዲሁም ከብዙ ዓመቶች ጀምሬም እናንተን ለመጐብኘት ከፍ ያለ ምኞት ስላለኝ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁን ግን በዚህ ሀገር ሥራዬን ስለ ጨረስሁ፥ ከብዙ ጊዜም ጀምሮ ወደ እናንተ ልመጣ እተጋ ስለ ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁን ግን በዚህ አገር ስፍራ ወደ ፊት ስለሌለኝ፥ ከብዙ ዓመትም ጀምሬ ወደ እናንተ ልመጣ ናፍቆት ስላለኝ፥ |
ይህም በተፈጸመ ጊዜ ጳውሎስ “ወደዚያ ደርሼ ሮሜን ደግሞ አይ ዘንድ ይገባኛል፤” ብሎ በመቄዶንያና በአካይያ አልፎ ወደ ኢየሩሳሌም እንዲሄድ በመንፈስ አሰበ።