La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሮሜ 14:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አንድን ቀን ከሌላው የተለየ አድርጎ የሚያስብ ሰው ለጌታ ብሎ ነው፤ የሚበላም ለጌታ ብሎ ይበላል፤ እግዚአብሔርን ያመሰግናልና የማይበላም ለጌታ ብሎ አይበላም፤ እግዚአብሔርንም ያመሰግናል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አንድን ቀን ከሌላው የተለየ አድርጎ የሚያስብ ሰው፣ እንዲህ የሚያደርገው ለጌታ ብሎ ነው፤ ሥጋ የሚበላውም ለጌታ ብሎ ይበላል፤ ለእግዚአብሔር ምስጋና ያቀርባልና። የማይበላም ለጌታ ሲል አይበላም፤ ለእግዚአብሔርም ምስጋና ያቀርባል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አንዱን ቀን ከሌላው ቀን አስበልጦ የሚያከብር ቢኖር ይህን ማድረጉ ለጌታ ክብር ብሎ ነው፤ ማንኛውንም ምግብ የሚበላ ለጌታ ክብር ብሎ ይበላል፤ ስለሚበላውም ምግብ እግዚአብሔርን ያመሰግናል፤ ማንኛውንም ምግብ የማይበላ ለጌታ ክብር ብሎ አይበላም፤ ባለመብላቱም እግዚአብሔርን ያመሰግናል።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አን​ዳ​ንድ ቀን የተ​ከ​ለ​ከ​ለም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተከ​ለ​ከለ፤ ዘወ​ትር የተ​ከ​ለ​ከ​ለም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተከ​ለ​ከለ፤ የበ​ላም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በላ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ያመ​ሰ​ግ​ነ​ዋል፤ ያል​በ​ላም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አል​በ​ላም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ያመ​ሰ​ግ​ነ​ዋል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ቀንን የሚያከብር ለጌታ ብሎ ያከብራል፤ የሚበላም እግዚአብሔርን ያመሰግናልና ለጌታ ብሎ ይበላል፤ የማይበላም ለጌታ ብሎ አይበላም እግዚአብሔርንም ያመሰግናል።

Ver Capítulo



ሮሜ 14:6
12 Referencias Cruzadas  

ይህም ቀን መታሰቢያ ይሁናችሁ፥ በዓል አድርጋችሁ ጠብቁት፥ ለጌታ በዓል ነው፤ ለትውልዳችሁ ለዘለዓለም ሥርዓት አድርጋችሁ ትጠብቁታላችሁ።


ከግብጽ ምድር ስላወጣቸው ለጌታ የተጠበቀች ሌሊት ናት፤ ይህች ሌሊት በእስራኤል ልጆች ሁሉ ዘንድ በትውልዳቸው ሁሉ ለጌታ የተጠበቀች ናት።


ሙሴም፦ “ዛሬ ብሉት፥ ዛሬ ለጌታ ሰንበት ነውና፤ ዛሬ በሜዳ አታገኙትም።


እኔ የመረጥሁት ጾም ይህ ነው? ሰውስ ነፍሱን የሚያዋርደው እንደዚህ ባለ ቀን ነው? በውኑ ራሱን እንደ እንግጫ ዝቅ እንዲያደርግ፥ ማቅንና አመድንም በበታቹ እንዲያነጥፍ ነው? በውኑ ይህን ጾም፥ በጌታ ዘንድ የተወደደ ቀን ብለህ ትጠራዋለህ?


በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ያሉ ምንቸቶችም ሁሉ ለሠራዊት ጌታ የተቀደሱ ይሆናሉ። የሚሠውትም ሰዎች ሁሉ ይመጣሉ፥ በእነርሱም ውስጥ ይቀቅሉባቸዋል። በዚያም ቀን በሠራዊት ጌታ ቤት ከእንግዲህ ወዲያ ነጋዴ አይገኝም።


ሕዝቡን በሣር ላይ እንዲቀመጡ አዘዘ፤ አምስቱንም እንጀራና ሁለቱን ዓሣ ይዞ ወደ ሰማይ አሻቅቦ አየና ባረከ፤ እንጀራውንም ቆርሶ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠ፤ ደቀ መዛሙርቱም ለሕዝቡ ሰጡ።


ሰባቱን እንጀራና ዓሣዎቹን ይዞ አመሰገነ፤ ቆርሶም ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠ፤ ደቀ መዛሙርቱም ለሕዝቡ ሰጡ።


እንግዲህ “የእግዚአብሔርን ሥራ ለመሥራት ምን እናድርግ?” አሉት።


ቀኖችን፥ ወሮችን፥ ዘመናትንና ዓመታትን በጥንቃቄ ትጠብቃላችሁ።