ሮሜ 14:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለአንተ ያለህ እምነት በእግዚአብሔር ፊት ለራስህ ይሁንልህ። ፈትኖ መልካም እንዲሆን በቆጠረው ነገር በራሱ ላይ የማይፈርድ የተባረከ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲያስ ስለ እነዚህ ነገሮች ያለህ እምነት በአንተና በእግዚአብሔር መካከል የተጠበቀ ይሁን፤ ትክክል ነው ብሎ በተቀበለው ነገር ራሱን የማይኰንን የተባረከ ሰው ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንግዲህ ይህ እምነትህ በአንተና በእግዚአብሔር መካከል ይሁን፤ ትክክል ነው ብሎ የሚያምንበትን ነገር ሲያደርግ ኅሊናው የማይወቅሰው ሰው የተመሰገነ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እምነት ካለህ በእግዚአብሔር ፊት ባመንኸው እምነት ራስህን አጽና፤ ባገኘው አእምሮም ራሱን የሚዘልፍ ብፁዕ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለአንተ ያለህ እምነት በእግዚአብሔር ፊት ለራስህ ይሁንልህ። ፈትኖ መልካም እንዲሆን በሚቍጥረው ነገር በራሱ ላይ የማይፈርድ ብፁዕ ነው። |
በራሱ ርኩስ የሆነ ነገር እንደሌለ በጌታ በኢየሱስ ሆኜ አውቄአለሁ፤ ተረድቼአለሁም፤ ነገር ግን ምንም ርኩስ እንዲሆን ለሚቆጥር ለእርሱ ርኩስ ነው።
ይህ ሰው አንድ ቀን ከሌላ ቀን እንደሚሻል ያስባል፤ ሌላው ግን ቀን ሁሉ አንድ እንደሆነ ያስባል፤ እያንዳንዱ በገዛ አእምሮው አጥብቆ ይረዳ።
ስለዚህ አንተ የምትፈርድ ሰው ሆይ! የምታመካኘው የለህም፤ በሌላው ላይ በምትፈርድበት ነገር በራስህ ላይ ትፈርዳለህ፤ ፈራጅ የሆንከው አንተ ያንኑ ታደርጋለህና።
ነገር ግን ይህ ዕውቀት በሁሉ ዘንድ አይገኝም፤ አንዳንዶች ግን ጣዖትን እስከ አሁን ድረስ ስለ ለመዱ፥ ለጣዖት የተሠዋ ነው፤ ብለው ይበላሉና፥ ሕሊናቸው ደካማ ስለ ሆነ ይረክሳል።
ትምክህታችን ይህ ነው፦ በዚህ ዓለም ይልቁንም በእናንተ ዘንድ፥ በእግዚአብሔር ጸጋ እንጂ በሥጋዊ ጥበብ ባልሆነ፥ በእግዚአብሔር ቅድስናና ቅንነት እንደኖርን፥ የሕሊናችን ምስክርነት ነው።
ወንድሞች ሆይ! ሰው ማንኛውንም ኃጢአት አድርጎ ቢገኝ፥ መንፈሳውያን የሆናችሁ እናንተ እንደዚህ ዓይነቱን ሰው በየውሃት መንፈስ አቅኑት፤ አንተም እንዳትፈተን ራስህን ጠብቅ።