ሮሜ 14:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በራሱ ርኩስ የሆነ ነገር እንደሌለ በጌታ በኢየሱስ ሆኜ አውቄአለሁ፤ ተረድቼአለሁም፤ ነገር ግን ምንም ርኩስ እንዲሆን ለሚቆጥር ለእርሱ ርኩስ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በጌታ በኢየሱስ ሆኜ በራሱ ንጹሕ ያልሆነ ምንም ምግብ እንደሌለ ተረድቻለሁ፤ ነገር ግን አንድ ሰው አንድን ነገር ንጹሕ እንዳልሆነ የሚቈጥር ከሆነ፣ ያ ነገር ለርሱ ንጹሕ አይደለም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንድን ነገር ርኩስ ነው ብሎ ለሚያስብ ሰው ያ ነገር ለእርሱ ርኩስ ይሆንበታል እንጂ ማንኛውም ነገር በራሱ ርኩስ እንዳልሆነ እኔ በጌታ ኢየሱስ ዐውቄ አረጋግጣለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በራሱ ርኩስ የሆነ ነገር እንደሌለ በጌታችን በኢየሱስ ሆኜ ዐውቄአለሁ፤ ተረድቼአለሁም፤ ነገር ግን ማናቸውም ነገር ርኩስ እንደሚሆን ለሚያስብ ያ ለእርሱ ርኩስ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በራሱ ርኵስ የሆነ ነገር እንደ ሌለ በጌታ በኢየሱስ ሆኜ አውቄአለሁ ተረድቼአለሁም፤ ነገር ግን ምንም ርኵስ እንዲሆን ለሚቆጥር ለእርሱ ርኵስ ነው። |
“አይሁዳዊ ሰው ከሌላ ወገን ጋር ይተባበር ወይም ይቃረብ ዘንድ እንዳልተፈቀደ እናንተ ታውቃላችሁ፤ ለእኔ ግን እግዚአብሔር ማንንም ሰው ‘ርኩስና የሚያስጸይፍ ነው’ እንዳልል አሳየኝ፤
አንተ ዕውቀት ያለህ በጣዖት ቤት በማዕድ ስትቀመጥ አንድ ሰው ቢያይህ፥ ደካማ ሰው ቢሆን ለጣዖት የተሠዋውን ለመብላት ሕሊናው አይደፋፈርምን?
ነገር ግን ይህ ዕውቀት በሁሉ ዘንድ አይገኝም፤ አንዳንዶች ግን ጣዖትን እስከ አሁን ድረስ ስለ ለመዱ፥ ለጣዖት የተሠዋ ነው፤ ብለው ይበላሉና፥ ሕሊናቸው ደካማ ስለ ሆነ ይረክሳል።
ለንጹሖች ሁሉ ነገር ንጹሕ ነው፤ ለርኩሳንና ለማያምኑ ግን ንጹሕ የሆነ ነገር ምንም የለም፤ ነገር ግን አእምሮአቸውም ሆነ ኅሊናቸው ረክሶአል።