ይህንኑ አሮጌ ልማዳቸውን እስከ አሁን ድረስ በመፈጸም ላይ ናቸው፤ እነርሱ እግዚአብሔርን አያመልኩም፤ ወይም ስሙ እስራኤል ተብሎ ለተጠራው ለያዕቆብ ልጆች እግዚአብሔር በሰጣቸው ደንቦች፥ ሥርዓቶች፥ ሕጎችና ትእዛዞች ጸንተው አልኖሩም።
ሮሜ 11:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህም “ዐይኖቻቸው እንዳያዩ፥ ጆሮቻቸውም እንዳይሰሙ፥ እግዚአብሔር ከባድ የእንቅልፍን መንፈስ እስከ ዛሬ ድረስ ሰጣቸው፤” ተብሎ ተጽፎአል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ፤ “ዐይናቸው እንዳያይ፣ ጆሯቸውም እንዳይሰማ፣ እግዚአብሔር እስከዚህ ቀን ድረስ፣ የድንዛዜ መንፈስ ሰጣቸው።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም “እግዚአብሔር ልቡናቸውን አደነዘዘ፤ ስለዚህ እስከ ዛሬ ድረስ በዐይናቸው አያዩም፤ በጆሮአቸውም አይሰሙም” ተብሎ እንደ ተጻፈው ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መጽሐፍ እንዳለ፥ “እስከ ዛሬ ድረስ በዐይናቸው እንዳያዩ በጆሮአቸውም እንዳይሰሙ እግዚአብሔር ደንዛዛ አእምሮን ሰጣቸው።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሌሎቹም ደነዘዙ፤ እንዲሁም፦ ዓይኖቻቸው እንዳያዩ ጆሮቻቸውም እንዳይሰሙ እግዚአብሔር የእንቅልፍ መንፈስን እስከ ዛሬ ድረስ ሰጣቸው ተብሎ ተጽፎአል። ዳዊትም፦ |
ይህንኑ አሮጌ ልማዳቸውን እስከ አሁን ድረስ በመፈጸም ላይ ናቸው፤ እነርሱ እግዚአብሔርን አያመልኩም፤ ወይም ስሙ እስራኤል ተብሎ ለተጠራው ለያዕቆብ ልጆች እግዚአብሔር በሰጣቸው ደንቦች፥ ሥርዓቶች፥ ሕጎችና ትእዛዞች ጸንተው አልኖሩም።
እነዚያ ሕዝቦች በዚሁ ዓይነት እግዚአብሔርን ማምለክ ጀመሩ፤ በሌላ በኩል ግን ለጣዖቶቻቸው ይሰግዱ ነበር፤ ዘሮቻቸውም እስከ ዛሬ ድረስ ይህንኑ ዓይነት አምልኮ እንደ ቀጠሉ ናቸው።
እርሱም እንዲህ አለኝ፤ “ወደዚህ ሕዝብ ሂድ፤ ‘መስማትን ትሰማላችሁ፤ ነገር ግን አታስተውሉም፤ ማየትንም ታያላችሁ፤ ነገር ግን ልብ አትሉም’ ብለህ ንገራቸው።
የሰው ልጅ ሆይ፥ በዓመፀኛ ቤት መካከል ተቀምጠሃል፥ እንዲያዩ ዐይን አላቸው ነገር ግን አያዩም፥ እንዲሰሙም ጆሮ አላቸው ነገር ግን አይሰሙም፥ እነርሱ ዓመፀኛ ቤት ናቸውና።
እርሱም “ለእናንተ የእግዚአብሔርን መንግሥት ምሥጢር ማወቅ ተሰጥቶአችኋል፤ ለሌሎች ግን እያዩ እንዳያዩ እየሰሙም እንዳያስተውሉ በምሳሌዎች ይነገራቸዋል” አላቸው።