ወደ ሰማይ የወጣ የወረደስ ማን ነው? ነፋስንስ በእጁ የጨበጠ ማን ነው? ውኃንስ በልብሱ የቋጠረ ማን ነው? የምድርን ዳርቻ ሁሉ ያጸና ማን ነው? ይህን ታውቅ እንደሆንህ፥ ስሙ ማን የልጁስ ስም ማን ነው?
ሮሜ 10:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእምነት የሆነው ጽድቅ ግን እንዲህ ይላል፥ “በልብህ ‘ወደ ሰማይ ማን ይወጣል?’ አትበል፤” ይህ ክርስቶስን ለማውረድ ነው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእምነት የሆነው ጽድቅ ግን እንዲህ ይላል፤ “ ‘በልብህ ማን ወደ ሰማይ ይወጣል?’ አትበል”፤ ይህ ክርስቶስን ለማውረድ ነው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሰዎችን በእምነት ስለ ማጽደቁ ግን እንዲህ ተብሎ ተጽፎአል፤ “በልብህ ወደ ሰማይ ማን ይወጣል?” አትበል፤ ይህም ክርስቶስን ለማውረድ ነው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእምነት ጽድቅ ግን እንዲህ ይላል፥ “በልብህ ወደ ሰማይ ማን ይወጣል?” አትበል፤ ከሰማይ የወረደው ክርስቶስ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእምነት የሆነ ጽድቅ ግን እንዲህ ይላል፦ በልብህ፦ ማን ወደ ሰማይ ይወጣል? አትበል፤ ይህ ክርስቶስን ለማውረድ ነው፤ |
ወደ ሰማይ የወጣ የወረደስ ማን ነው? ነፋስንስ በእጁ የጨበጠ ማን ነው? ውኃንስ በልብሱ የቋጠረ ማን ነው? የምድርን ዳርቻ ሁሉ ያጸና ማን ነው? ይህን ታውቅ እንደሆንህ፥ ስሙ ማን የልጁስ ስም ማን ነው?
ከሰማይ የወረደው እንጀራ ይህ ነው፤ አባቶቻችሁ በልተው ነገር ግን እንደሞቱበት ዓይነት አይደለም፤ ይህን እንጀራ የሚበላ ለዘለዓለም ይኖራል።”
እርሱንም እግዚአብሔር በእምነት የሚገኝ በደሙም የሆነ ማስተስሪያ አድርጎ ያቀረበው ነው፤ ይህም በእግዚአብሔር ትዕግስት በፊት የተደረገውን ኃጢአት በመተው ጽድቁን እንዲያሳይ ነው፤
በክርስቶስም በማመን በእምነት ላይ የተመሠረተውን የእግዚአብሔርን ጽድቅ እንጂ በሕግ ላይ የተመሠረተውን የራሴ ጽድቅ ሳይኖረኝ፥ በእርሱ እንድገኝ ነው፤
ኖኅ ገና ስለማይታየው ነገር ተረድቶ እግዚአብሔርን እየፈራ ቤተ ስዎቹን ለማዳን መርከብን በእምነት አዘጋጀ፤ በዚህም ዓለምን ኰነነ፤ በእምነትም የሚገኘውን ጽድቅ ወራሽ ሆነ።