ነገር ግን ሲሰናበታቸው “የሚመጣውን በዓል በኢየሩሳሌም አደርግ ዘንድ ይገባኛል እግዚአብሔር ቢፈቅድ ግን ወደ እናንተ ደግሞ እመለሳለሁ፤” አላቸው። ከኤፌሶንም በመርከብ ተነሣ።
ሮሜ 1:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምናልባት አሁን በመጨረሻ፥ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ወደ እናንተ ለመምጣት ሁልጊዜ በጸሎቴ እጠይቃለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በጸሎቴ ሁልጊዜ አስባችኋለሁ፤ አሁን ደግሞ በመጨረሻ በእግዚአብሔር ፈቃድ ወደ እናንተ እንድመጣ መንገድ ይከፈትልኝ ዘንድ እጸልያለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደግሞ አሁን በመጨረሻ ወደ እናንተ ለመምጣት የእግዚአብሔር ፈቃድ ሆኖ መንገዴ እንዲቃናልኝ ሁልጊዜ እጸልያለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ እናንተ እመጣ ዘንድም እግዚአብሔር በፈቃዱ መንገዴን ያቃናልኝ ዘንድ ዘወትር እጸልያለሁ። |
ነገር ግን ሲሰናበታቸው “የሚመጣውን በዓል በኢየሩሳሌም አደርግ ዘንድ ይገባኛል እግዚአብሔር ቢፈቅድ ግን ወደ እናንተ ደግሞ እመለሳለሁ፤” አላቸው። ከኤፌሶንም በመርከብ ተነሣ።
ይህም በተፈጸመ ጊዜ ጳውሎስ “ወደዚያ ደርሼ ሮሜን ደግሞ አይ ዘንድ ይገባኛል፤” ብሎ በመቄዶንያና በአካይያ አልፎ ወደ ኢየሩሳሌም እንዲሄድ በመንፈስ አሰበ።