በዚህም ጊዜ ኢዩ ወደ ኢይዝራኤል ደረሰ፤ ኤልዛቤልም ይህን የሆነውን ነገር ሰምታ ዐይንዋን ተኳለች፤ ጠጉርዋንም ተሠርታ በቤተ መንግሥቱ ሰገነት ላይ በመስኮት አዘንብላ ቁልቁል መንገዱን ትመለከት ነበር።
ራእይ 9:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሴቶችን ጠጉር የሚመስል ጠጉር ነበራቸው፤ ጥርሳቸውም እንደ አንበሳ ጥርስ ነበረ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጠጕራቸው የሴት ጠጕር፣ ጥርሳቸውም የአንበሳ ጥርስ ይመስል ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሴት ጠጒር የመሰለ ጠጒር ነበራቸው፤ ጥርሳቸው የአንበሳ ጥርስ ይመስል ነበር፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሴቶችን ጠጕር የሚመስል ጠጕር ነበራቸው፤ ጥርሳቸውም እንደ አንበሳ ጥርስ ነበረ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሴቶችን ጠጕር የሚመስል ጠጕር ነበራቸው፥ ጥርሳቸውም እንደ አንበሳ ጥርስ ነበረ፥ |
በዚህም ጊዜ ኢዩ ወደ ኢይዝራኤል ደረሰ፤ ኤልዛቤልም ይህን የሆነውን ነገር ሰምታ ዐይንዋን ተኳለች፤ ጠጉርዋንም ተሠርታ በቤተ መንግሥቱ ሰገነት ላይ በመስኮት አዘንብላ ቁልቁል መንገዱን ትመለከት ነበር።
ደግሞም ኢሳይያስ “የሠራዊት ጌታ ዘር ባያስቀርልን ኖሮ፥ እንደ ሰዶም በሆንን ነበር፥ ገሞራንም በመሰልን ነበር” ብሎ አስቀድሞ እንደ ተናገረው ነው።
እንዲሁም ደግሞ ሴቶች ከትሕትናና ራስን ከመግዛት ጋር በሚገባ ልብስ ራሳቸውን ያስጊጡ፤ ይሁንና በቄንጠኛ የጸጉር አሠራር ወይም በወርቅ ወይም በዕንቁ ወይም ዋጋው እጅግ በከበረ ልብስ አይሁን።