ቀኑ በመሸ ጊዜ፥ የጌታ እግዚአብሔርን ድምፅ ከገነት ውስጥ ሲመላለስ ሰሙ፥ አዳምና ሚስቱ ከጌታ እግዚእብሔር ፊት በገነት ዛፎች መካከል ተሸሸጉ።
ራእይ 6:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም፥ ሀብታሞችም፥ ኃይለኞችም፥ አገልጋዮችም፥ ጌቶችም ሁሉ በዋሻዎችና በተራራዎች ዐለቶች ውስጥ ተሰወሩ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ በኋላ የምድር ነገሥታትና ገዦች፣ የጦር መኰንኖች፣ ሀብታሞች፣ ብርቱዎች፣ ባሮችና ጌቶች ሁሉ በዋሻዎችና በተራሮች ዐለት ውስጥ ተሸሸጉ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የምድር ነገሥታት፥ ገዢዎች፥ የጦር አለቆች፥ ሀብታሞች፥ ኀይለኞች፥ አገልጋዮችና ጌቶችም ሁሉ በዋሻዎችና በተራራዎች አለቶች ውስጥ ተሸሸጉ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኀይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዐለቶች ተሰወሩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ፥ |
ቀኑ በመሸ ጊዜ፥ የጌታ እግዚአብሔርን ድምፅ ከገነት ውስጥ ሲመላለስ ሰሙ፥ አዳምና ሚስቱ ከጌታ እግዚእብሔር ፊት በገነት ዛፎች መካከል ተሸሸጉ።
ጌታ ምድርን ለማናወጥ በሚነሣበት ጊዜ፤ ሰዎች ከአስፈሪነቱ እንዲሁም ከግርማው የተነሣ፤ ወደ ድንጋይ ዋሻ፤ ወደ ዐለት ስንጣቂ ሮጠው ይገባሉ።
ይህ ግን የተበዘበዘና የተዘረፈ ሕዝብ ነው፤ ሁሉም በዋሻ ውስጥ ተጠምደዋል፤ በግዞት ቤትም ተሸሽገዋል፤ ተበዝብዘዋል የሚያድንም የለም፥ ተማርከዋል፤ “መልሷቸው” የሚል ማንም የለም።
እንደ እባብ አፈር ይልሳሉ፥ በምድር እንደሚሳቡ ፍጥረታት እየተንቀጠቀጡ ከምሽጋቸው ይመጣሉ፤ በፍርሃት ወደ ጌታ አምላካችን ይመጣሉ፥ ከአንተ የተነሣ ይፈራሉ።
የመብራትም ብርሃን ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይበራም፤ የሙሽራውና የሙሽራይቱም ድምጽ ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይሰማም፤ ነጋዴዎችሽ የምድር መኳንንት ነበሩና፤ በአስማትሽም አሕዛብ ሁሉ ስተዋልና።”
እስራኤላውያን ያሉበት ሁኔታ እጅግ አስጊ መሆኑንና ሠራዊታቸውም በከባድ ጭንቀት ውስጥ መግባቱን ባዩ ጊዜ፥ በየዋሻውና በየቁጥቋጦው፥ በየዐለቱ መካከልና በየገደሉ እንዲሁም በየጉድጓዱ ሁሉ ተሸሸጉ።