ራእይ 6:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጉም ከሰባቱ ማኅተሞች አንዱን በፈታ ጊዜ አየሁ፤ ከአራቱም ሕያዋን ፍጡራን አንዱ ነጐድጓድ በሚመስል ድምፅ “ና” ሲል ሰማሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በጉም ከሰባቱ ማኅተሞች የመጀመሪያውን ሲፈታ አየሁ፤ ከዚያም ከአራቱ ሕያዋን ፍጡራን አንዱ፣ ነጐድጓድ በሚመስል ድምፅ “ና!” ሲል ሰማሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በኋላ በጉ ከሰባቱ ማኅተሞች የመጀመሪያውን ሲከፍት አየሁ። ከአራቱ እንስሶች አንዱ እንደ ነጐድጓድ በሚያስገመግም ድምፅ “ና!” ሲል ሰማሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በጉም ከሰባቱ ማኅተም አንዱን በፈታ ጊዜ አየሁ፤ ከአራቱም እንስሶች አንዱ ነጐድጓድ በሚመስል ድምፅ “መጥተህ እይ” ሲል ሰማሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በጉም ከሰባቱ ማኅተም አንዱን በፈታ ጊዜ አየሁ፥ ከአራቱም እንስሶች አንዱ ነጐድጓድ በሚመስል ድምፅ፦ መጥተህ እይ ሲል ሰማሁ። |
በሰማይም ያለው የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ተከፈተ፤ የኪዳኑም ታቦት በቤተ በመቅደሱ ታየ፤ መብረቅና ድምፅም ነጐድጓድም የምድርም መናወጥ ታላቅም በረዶ ሆነ።
ከሰማይም እንደ ብዙ ውሃ ድምፅና እንደ ታላቅ ነጐድጓድ ድምፅ የመሰለ ድምፅን ሰማሁ፤ የሰማሁትም ድምፅ ደርዳሪዎች በበገናቸው ሲደረድሩ እንደሚሰማው ዓይነት ድምፅ ነበር።
የብዙ ሕዝብም ድምፅ፥ የብዙ ውሃዎችም ድምፅ፥ የብርቱም ነጐድጓድም ድምፅ የሚመስል ድምፅ እንዲህ ሲል ሰማሁ፤ “ሃሌ ሉያ! ሁሉን የሚገዛ ጌታ አምላካችን ነግሦአልና።
አራቱም ሕያዋን ፍጡራን እያንዳንዳቸው ስድስት ክንፎች አሉአቸው፤ በዙሪያቸውና በውስጣቸውም ዐይኖች ሞልተውባቸዋል፤ “ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የነበረውና ያለ የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ” ከማለት ቀንና ሌሊት አያርፉም ነበር።
መጽሐፉንም በወሰደ ጊዜ አራቱ ሕያዋን ፍጡራን ሃያ አራቱ ሽማግሌዎች በበጉ ፊት ወደቁ፤ እያንዳንዳቸውም በገናንና የቅዱሳን ጸሎት የሆነ ዕጣን የሞላበትን የወርቅ ሳሕን ያዙ።
ሦስተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ ሦስተኛው እንስሳ “ና” ሲል ሰማሁ። አየሁም፤ እነሆም ጥቁር ፈረስ ወጣ፤ በእርሱም ላይ የተቀመጠው በእጁ ሚዛን ያዘ።