ራእይ 21:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቅጥርዋም ከኢያሰጲድ የተሠራ ነበረ፤ ከተማይቱም የጠራ ብርጭቆ የሚመስል ንጹሕ ወርቅ ነበረች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቅጥሩ የተሠራው ከኢያሰጲድ ነበር፤ ከተማዪቱም እንደ መስተዋት ንጹሕ ከሆነ ወርቅ የተሠራች ነበረች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ግንቡም የተሠራው ከኢያሰጲድ ነበረ፤ ከተማይቱም እንደ መስተዋት በጠራ በንጹሕ ወርቅ የተሠራች ነበረች፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቅጥርዋም ከኢያሰጲድ የተሠራ ነበረ፤ ከተማይቱም ጥሩ ብርጭቆ የሚመስል ጥሩ ወርቅ ነበረች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቅጥርዋም ከኢያሰጲድ የተሠራ ነበረ፥ ከተማይቱም ጥሩ ብርጭቆ የሚመስል ጥሩ ወርቅ ነበረች። |
የከተማይቱም ቅጥር መሠረቶች በከበረ ድንጋይ ሁሉ ያጌጦ ነበር፤ የመጀመሪያው መሠረት ኢያሰጲድ፥ ሁለተኛው ሰንፔር፥ ሦስተኛው ኬልቄዶን፥ አራተኛው መረግድ፥
ዐሥራ ሁለቱም ደጆች ዐሥራ ሁለት ዕንቁዎች ነበሩ፤ እያንዳንዱም ደጅ ከአንድ ዕንቁ የተሠራ ነበረ። የከተማይቱም መንገድ እንደ መስታወት ብርሃን ከሚያስተላልፍ ከንጹሕ ወርቅ የተሠራ ነበረ።
በዙፋኑም ፊት ብርሌ የሚመስል የብርጭቆ ባሕር ነበረ። በዙፋኑም መካከል በዙፋኑም ዙሪያ፥ በፊትና በኋላ ዐይኖች የሞሉአቸው አራት ሕያዋን ፍጡራን ነበሩ።