ራእይ 10:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የተከፈተችንም ትንሽ መጽሐፍ በእጁ ይዞ ነበር። ቀኝ እግሩንም በባሕር ላይ ግራውንም በምድር ላይ አኖረ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእጁም የተከፈተች ትንሽ ጥቅልል መጽሐፍ ይዞ ነበር፤ ቀኝ እግሩን በባሕር ላይ፣ ግራ እግሩን በምድር ላይ አኖረ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የተከፈተች ትንሽ የብራና ጥቅል መጽሐፍ በእጁ ይዞ ነበር፤ ቀኝ እግሩን በባሕር ላይ፥ ግራ እግሩንም በምድር ላይ አኖረ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የተከፈተችንም ታናሽ መጽሐፍ በእጁ ያዘ። ቀኝ እግሩንም በባሕር ላይ ግራውንም በምድር ላይ አኖረ፤ እንደሚያገሣም አንበሳ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የተከፈተችንም ታናሽ መጽሐፍ በእጁ ያዘ። ቀኝ እግሩንም በባሕር ላይ ግራውንም በምድር ላይ አኖረ፥ እንደሚያገሣም አንበሳ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። |