ዘመናችን ሁሉ አልፎአልና፥ እኛም በመዓትህ አልቀናልና፥ ዘመኖቻችንንም እንደ ትንፋሽ ይሆናሉ።
ዘመናችን ሁሉ በቍጣህ ዐልፏልና፤ ዕድሜያችንንም በመቃተት እንጨርሳለን።
ዘመናችን ሁሉ በቊጣህ ያልፋሉ የዕድሜአችንም ፍጻሜ እንደ እስትንፋስ ነው።
አቤቱ፥ አንተ ተስፋዬ ነህና፤ ልዑልን መጠጊያህ አደረግህ።
በነፋስ ፊት እንዳለ ትቢያ ይሁኑ፥ የጌታም መልአክ ያስጨንቃቸው።
በተግሣጽህ ስለ ኃጢአቱ ሰውን ዘለፍኸው፥ የሚመኘውንም እንደ ብል ታጠፋበታለህ፥ በእውነት ሰው ሁሉ ከንቱ ነው።
አቤቱ፥ ፍጻሜዬን አስታውቀኝ፥ የዘመኔ ቁጥሮች ምን ያህል እንደ ሆኑ፥ እኔ ምን ያህል ረጋፊ እንደሆንኩ አውቅ ዘንድ።
ቀኖቻቸውም በከንቱ አለቁ፥ ዓመቶቻቸውም በሽብር።
ሺህ ዓመት በፊትህ እንዳለፈች እንደ ትናንት ቀን፥ እንደ ሌሊትም ጥቂት ሰዓት ነውና።