መዝሙር 89:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ፥ ጽኑ ፍቅርህን ለዘለዓለም እዘምራለሁ፥ እውነትህንም በአፌ ለልጅ ልጅ እናገራለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምሕረትህን ለዘላለም እንደምትመሠርት፣ ታማኝነትህንም በሰማይ እንደምታጸና እናገራለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፍቅርህ ለዘለዓለም እንደሚጸናና ታማኝነትህን እንደ ሰማይ እንደሚመሠረት እናገራለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ተራሮች ሳይወለዱ፥ ምድርም ዓለምም ሳይሠሩ፥ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ድረስ መቼም መች አንተ ነህ። |
ለመስማትም እንቢ አሉ፥ በመካከላቸው ያደረግኸውን ተአምራት አላስታወሱም፤ አንገታቸውንም አደነደኑ፥ በዓመፃቸውም ወደ ባርነታቸው ለመመለስ መሪ ሾሙ፤ አንተ ግን ይቅር ባይ አምላክ፥ ቸር፥ ርኅሩኅ፥ ለቁጣ የዘገየህና ምሕረትህ የበዛ ነህ፥ አልተውካቸውምም።”
ሐሰትን ይናገር ዘንድ እግዚአብሔር ሰው አይደለም፥ ይጸጸትም ዘንድ የሰው ልጅ አይደለም። እርሱ ያለውን አያደርገውምን? የተናገረውንስ አይፈጽመውምን?
ይሄውም እግዚአብሔር ሊዋሽ በማይቻል በሁለት በማይለወጥ ነገር፥ በፊታችን ያለውን ተስፋ ለመያዝ ለሸሸን ለእኛ ብርቱ መጽናናት እንዲሆንልን ነው።