ሁልጊዜ እንደ ውኃ ከበቡኝ፥ በአንድ ላይም አጥለቀለቁኝ።
ወዳጄንና ባልንጀራዬን ከእኔ አራቅህ፤ ጓደኛዬ ጨለማ ብቻ ሆኖ ቀረ።
የቅርብ ወዳጆቼንና ጓደኞቼን ከእኔ አርቀህ ጨለማ ብቻ ከእኔ ጋር እንዲቀር አደረግህ።
ረድኤታችን ከእግዚአብሔር ነውና። ንጉሣችንም የእስራኤል ቅዱስ ነውና።
አሕዛብ ሁሉ ከበቡኝ፥ በጌታ ስም አጠፋኋቸው፥
መክበቡንስ ከበቡኝ፥ በጌታ ስም አጠፋኋቸው።
ሕይወቴ በኅዘን አልቃለችና፥ ዓመታቴም በልቅሶ ጩኸት፥ ኃይሌ በችግር ደከመ፥ አጥንቶቼም ተነዋወጡ።
ልቤ ደነገጠብኝ፥ ኃይሌም ተወችኝ፥ የዐይኖቼም ብርሃን ፈዘዘ።
በእኔ ላይ ቁጣህ ጸና፥ ማዕበልህንም ሁሉ በእኔ ላይ አመጣህ።