ነገር ግን የእስራኤል አምላክ ጌታ በእስራኤል ላይ የዘለዓለም ንጉሥ እንድሆን ከአባቴ ቤት ሁሉ መርጦኛል፤ ይሁዳንም አለቃ እንዲሆን መርጦታል፤ ከይሁዳም ቤት የአባቴን ቤት መርጦአል፤ ከአባቴም ልጆች መካከል በእስራኤል ሁሉ ላይ ሊያነግሠኝና ሊመርጠኝ ወደደ።
መዝሙር 78:68 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የይሁዳን ወገን ግን መረጠ፥ የወደደውን የጽዮንን ተራራ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን የይሁዳን ነገድ፣ የወደዳትን የጽዮንን ተራራ መረጠ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን የይሁዳን ነገድና በጣም የሚወዳትን የጽዮንን ተራራ መረጠ። |
ነገር ግን የእስራኤል አምላክ ጌታ በእስራኤል ላይ የዘለዓለም ንጉሥ እንድሆን ከአባቴ ቤት ሁሉ መርጦኛል፤ ይሁዳንም አለቃ እንዲሆን መርጦታል፤ ከይሁዳም ቤት የአባቴን ቤት መርጦአል፤ ከአባቴም ልጆች መካከል በእስራኤል ሁሉ ላይ ሊያነግሠኝና ሊመርጠኝ ወደደ።
ጌታ ሳሙኤልን፥ “በእስራኤል ላይ እንዳይነግሥ ለናቅሁት ለሳኦል የምታለቅስለት እስከ መቼ ነው? ወደ ቤተልሔሙ ሰው ወደ እሴይ ስለምልክህ፥ ዘይት በቀንድ ሞልተህ ሂድ፤ ከልጆቹ አንዱ ንጉሥ ይሆን ዘንድ መርጬዋለሁ” አለው።