ዝንቦችንም በላያቸው ሰደደባቸው፥ በሉአቸውም፥ በጓጉንቸርም አጠፋቸው።
የዝንብ ሰራዊት ሰደደባቸው፤ ነደፏቸውም፤ ጓጕንቸርም ላከባቸው፤ ሰዎችንም አጠፉ።
እነርሱን የሚያሠቃዩ ዝንቦችንና ጥፋትን የሚያስከትሉ እንቊራሪቶችን ወደ እነርሱ ላከ።
ሕዝቤን ባትለቅቅ፥ እነሆ በአንተ ላይ፥ በአገልጋዮችህ ላይ፤ በሕዝብህ ላይ፥ በቤቶችህም ላይ የዝንብ መንጋ እልካለሁ፤ የግብፃውያንም ቤቶች፥ የቆሙባትም ምድር ሁሉ በዝንብ መንጋ ይሞላሉ።
ጌታም እንዲሁ አደረገ፤ በፈርዖን ቤት፥ በአገልጋዮቹም ቤቶች ውስጥ ብዙ የዝንብ መንጋ መጣ፤ በግብጽም ምድር ሁሉ ላይ፤ ከዝንቡ መንጋ የተነሣ ምድር ተበላሸች።
ሁለተኛውም መልአክ ጽዋውን በባሕር ውስጥ አፈሰሰ፤ ባሕሩም የሞተ ሰው ደም መሰለ፤ በባሕርም ውስጥ ሕይወት ያለው ነፍስ ሁሉ ሞተ።