የመላክትንም እንጀራ ሰው በላ ስንቅንም እስኪተርፋቸው ላከላቸው።
ሰዎች የኀያላንን እንጀራ በሉ፤ ጠግበው እስከሚተርፍ ድረስ ምግብ ላከላቸው።
በዚህ ዐይነት ሰዎች የመላእክትን እንጀራ በሉ፤ እግዚአብሔር የሚፈልጉትን ምግብ ሁሉ ሰጣቸው።
ቃሉን የምትፈጽሙ መላእክቱ፥ ብርቱዎችና ኃያላን፥ የቃሉንም ድምፅ የምትሰሙ ሁሉ፥ ጌታን ባርኩ።
ለመኑ፥ ድርጭትንም አመጣላቸው፥ የሰማይንም እንጀራ አጠገባቸው።
ሙሴም፦ “ጌታ በማታ የምትበሉትን ሥጋና በማለዳ ደግሞ የሚያጠግባችሁን ምግብ ሲሰጣችሁ ጌታ ያጉረመረማችሁበትን ማጉረምረም ሰምቶ ነው፤ እኛ ምንድን ነን? ማጉረምረማችሁ በጌታ ላይ ነው እንጂ በእኛ ላይ አይደለም” አለ።
ሁሉም በልተው ጠገቡ፤ የተረፈውንም ቁርስራሽ ዐሥራ ሁለት መሶብ ሙሉ አነሡ።
ሁሉም በልተው ጠገቡ፤ የተረፈውንም ቁርስራሽ ሰባት ቅርጫት ሙሉ አነሡ።