መዝሙር 76:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ድንኳኑ በሳሌም፥ ማደሪያውም በጽዮን ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያም ተወርዋሪውን ፍላጻ፣ ጋሻንና ሰይፍን፣ ጦርንም ሰበረ። ሴላ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያም የሚያንጸባርቁ ፍላጻዎችን፥ ጋሻና ጦርን፥ ሌሎችንም የጦር መሣሪያዎች ሁሉ ሰባበረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርን ዐሰብሁት፥ ደስ አለኝም፤ ተናገርሁ፥ ነፍሴም ፈዘዘች። የጠላቶቼን ሁሉ ሰዓቶች ዐወቅኋቸው |
ኢዮሣፍጥና ሕዝቡም ምርኮ ለመውሰድ መጡ፤ ብዙ ከብትና ልዩ ልዩ ዕቃም፥ ልብስም፥ እጅግም ያማረ ዕቃ አገኙ፥ በዘበዙትም፥ ሁሉንም ለመሸከም አልቻሉም፤ ከምርኮውም ብዛት የተነሣ እስከ ሦስት ቀን ድረስ ይበዘብዙ ነበር።
ጌታም ጽኑዓን ኃያላኑንና መሳፍንቱን የጦር አዛዦቹንም ከአሦር ንጉሥ ሰፈር እንዲያጠፋ መልአኩን ላከ። የአሦርም ንጉሥ አፍሮ ወደ አገሩ ተመለሰ። ወደ አምላኩም ቤት በገባ ጊዜ ከአብራኩ የወጡት ልጆቹ በዚያ በሰይፍ ገደሉት።