መዝሙር 73:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆ፥ ከአንተ የሚርቁ ይጠፋሉና፥ በማመንዘር ከአንተ የሚርቁትን ሁሉ አጠፋኻቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነሆ፤ ከአንተ የሚርቁ ይጠፋሉና፤ አንተ የሚያመነዝሩትን ሁሉ ታጠፋቸዋለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነሆ፥ ከአንተ የሚርቁ ይጠፋሉ፤ አንተን የሚክዱህን ሁሉ ትደመስሳቸዋለህ። |
አምላኮቻቸውን ተከትለው ባመነዘሩና በሠዉላቸው ጊዜ እንዳይጠሩህና ከመሥዋዕታቸው እንዳትበላ፥ በምድሪቱ ከሚኖሩ ሰዎች ጋር ቃል ኪዳን እንዳታደርግ፥
ጌታም፦ ይህ ሕዝብ በአፉ ወደ እኔ ይቀርባል፥ በከንፈሮቹም ያከብረኛል፥ ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነው፤ በሰዎች ሥርዓትና ትምህርት ብቻ ይፈራኛል።
ዘርፉንም በልብሳችሁ ላይ አኑሩት እርሱንም በተመለከታችሁ ጊዜ የጌታን ትእዛዝ ሁሉ ታስታውሳላችሁ ታደርጉታላችሁም፥ ምኞታችሁንም በመከተል ያመነዘራችሁባትን የልባችሁንና የዐይኖቻችሁን ፈቃድ የማትከተሉ ትሆናላችሁ።
አመንዝሮች ሆይ! ከዓለም ጋር ወዳጅ መሆን የእግዚአብሔር ጠላትነት መሆኑን አታውቁምን? ስለዚህ የዓለም ወዳጅ መሆን የሚፈልግ ሁሉ የእግዚአብሔር ጠላት ሆኖአል።