La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መዝሙር 71:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

“እግዚአብሔር ትቶታል፥ የሚያድነው የለምና ተከትላችሁ ያዙት።”

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እነርሱም፣ “እግዚአብሔር ትቶታል፤ የሚያስጥለው የለምና፣ ተከታትላችሁ ያዙት” አሉ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“እግዚአብሔር ትቶታል፤ ተከታትለን እንያዘው፤ የሚያድነው ማንም የለም” ይላሉ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የም​ድር ነገ​ሥ​ታት ሁሉ ይሰ​ግ​ዱ​ለ​ታል ፥ አሕ​ዛ​ብም ሁሉ ይገ​ዙ​ለ​ታል።

Ver Capítulo



መዝሙር 71:11
13 Referencias Cruzadas  

አቤቱ፥ የሚያስጨንቁኝ ምንኛ በዙ! በኔ ላይ የሚቆሙት ብዙ ናቸው።


ጐለመስሁ አረጀሁም፥ ጻድቅ ሲጣል፥ ዘሩም እህል ሲለምን አላየሁም።


ጌታ ፍርድን ይወድዳልና፥ ቅዱሳኑንም አይጥላቸውምና፥ ለዘለዓለምም ይጠብቃቸዋል ለንጹሓንም ይበቀልላቸዋል፥ የክፉዎች ዘር ግን ይጠፋል።


እግዚአብሔርን፦ አንተ መጠጊያዬ ነህ፥ ለምን ረሳኸኝ? ጠላቶቼ ሲያስጨንቁኝ ለምን አዝኜ እመላለሳለሁ? እለዋለሁ።


እግዚአብሔርን የምትረሱ እናንተ፥ ይህን አስተውሉ፥ አለዚያ ግን ስበታትናችሁ የሚያድንም የለም።


አቤቱ አምላኬ፥ በአንተ ታመንሁ፥ ከሚያሳድዱኝ ሁሉ አድነኝና አውጣኝ፥


በዘጠኝ ሰዓት አካባቢ ኢየሱስ “ኤሊ ኤሊ ላማ ሰበቅታኒ?” ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። ይህም “አምላኬ አምላኬ፥ ለምን ተውከኝ?” ማለት ነው።


የተቀሩት ግን “ተወው፤ ኤልያስ መጥቶ ያድነው እንደሆነ እንይ” አሉ።


ሳኦል የዳዊትን ወደ ቅዒላ መሄድ በሰማ ጊዜ፥ “ዳዊት መዝጊያና የብረት መወርወሪያ ወዳላት ከተማ መግባቱ፥ ራሱን በራሱ እንደ ማሰር ስለ ሆነ፥ ይህን ሰው እግዚአብሔር በእጄ አሳልፎ ቢሰጠኝ ነው” አለ።