ጥሩርና ጋሻ ያዝ፥ እኔንም ለመርዳት ተነሥ።
ትልቁንና ትንሹን ጋሻ ያዝ፤ እኔንም ለመርዳት ተነሥ።
ጋሻና ጥሩር ያዝ፤ መጥተህም እርዳኝ።
በአንደበቱ ሸንግሎአልና፤ ኀጢአቱ ባገኘችው ጊዜ ይጠላታል።
በላባዎቹ ይጋርድሃል፥ ከክንፎቹም በታች ትጠለላለህ፥ ታማኝነቱ እንደ ጋሻና እንደ ቅጥር ይከብብሃል።
ጌታ ተዋጊ ነው፥ ስሙም ጌታ ነው፤
ጌታና የቁጣው ጦር መሣሪያ፤ ምድሪቱን በሙሉ ለማጥፋት፤ ከሩቅ አገር፤ ከሰማያትም ዳርቻ መጥተዋል።
ጌታ እንደ ኃያል ይወጣል እንደ ሰልፈኛም ቅንዓትን ያስነሣል፤ ይጮኻል ድምፁንም ያሰማል በጠላቶቹም ላይ ይበረታል።