አቤቱ፥ እስከ መቼ ድረስ ዝም ብለህ ታየኛለህ? ነፍሴን ከክፉ ሥራቸው ብቸኛዪቱንም ከአንበሶች አድናት።
ጌታ ሆይ፤ እስከ መቼ ዝም ብለህ ታያለህ? ነፍሴን ከክፉ ሥራቸው፣ ብርቅ ሕይወቴን ከአንበሶች ታደጋት።
እግዚአብሔር ሆይ! እስከ መቼ ድረስ ዝም ብለህ ታየኛለህ? ከክፉ ሥራቸው አድነኝ፤ ከእነዚህ እንደ አንበሳ ጨካኝ ከሆኑ ሰዎች ታደገኝ!
አየኸው፥ አንተ ክፋትንና ቁጣን ትመለከታለህና በእጅህ ፍዳውን ለመስጠት፥ ምስኪን እራሱን ለአንተ አሳልፎ ይሰጣል፥ ለድሀ አደግም ረዳቱ አንተ ነህ።
ከሰማይ ልኮ አዳነኝ፥ ለረገጡኝም ውርደትን ሰጣቸው፥ እግዚአብሔር ቸርነቱንና እውነቱን ላከ።
ዝያለሁና አቤቱ፥ ማረኝ፥ አጥንቶቼ ታውከዋልና ፈውሰኝ።
ዕድሜውንም አሳጠርህ፥ በእፍረትም ሸፈንኸው።
ዐይኖችህ ክፉ እንዳያዩ እጅግ ንጹሐን ናቸው፥ ክፉ ሥራም መመልከት አትችልም፤ አታላዮችን ለምን ትመለከታለህ? ክፉዎቹ ከእርሱ ይልቅ ጻድቅ የሆኑትን ሲውጡ ለምን ዝም ትላለህ?