አቤቱ፥ እስራኤልን ከመከራው ሁሉ አድነው።
አምላክ ሆይ፤ እስራኤልን ከመከራው ሁሉ አድነው።
አምላክ ሆይ! እስራኤልን ከመከራው ሁሉ አድን!
ለኢየሩሳሌም ሰላምን ለምኑ፥ አንተንም ለሚወድዱ መረጋጋት ይሁን።
እርሱም እስራኤልን ከበደሉ ሁሉ ያድነዋል።
ከጽዮን መድኃኒትን ለእስራኤል ማን ይሰጣል? ጌታ የሕዝቡን ምርኮ በመለሰ ጊዜ፥ ያዕቆብ ደስ ይለዋል፥ እስራኤልም ሐሤት ያደርጋል።
በጭንቃቸው ሁሉ እርሱ ተጨነቀ፥ የፊቱም መልአክ አዳናቸው፤ በፍቅሩና በርኅራኄውም ተቤዣቸው፥ በቀደመውም ዘመን ሁሉ አንሥቶ ተሸከማቸው።