መዝሙር 25:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ለሚፈሩት ወዳጃቸው ነው፥ ቃል ኪዳኑንም ያስታውቃቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ምስጢሩን ከሚፈሩት ወዳጆቹ አይሰውርም፤ ኪዳኑንም ይገልጥላቸዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ለሚታዘዙት ሁሉ ወዳጃቸው ነው፤ ለእነርሱ የገባውንም ቃል ኪዳን ያጸናል። |
እርሱም ዓለም ሊቀበለው የማይቻለው የእውነት መንፈስ ነው፤ ምክንያቱም ዓለም ስለማያየውና ስለማያውቀው ነው። ነገር ግን በእናንተ ዘንድ ስለሚኖር፥ በውስጣችሁም ስለሚሆን እናንተ ታውቁታላችሁ።
ከእንግዲህ ወዲህ ባሮች አልላችሁም፤ ባርያ ጌታው የሚያደርገውን አያውቅምና፤ ወዳጆች ግን ብያችኋለሁ፤ ከአባቴ የሰማሁትን ሁሉ ለእናንተ አስታውቄአችኋለሁና።
ፍጥረታዊ ሰው ግን የእግዚአብሔርን መንፈስ ነገር አይቀበለውም፤ ይህ ለእርሱ ሞኝነት ነው፥ ምክንያቱም በመንፈስ የሚመረመር ነውና፥ ሊያውቀው አይችልም።
በእርሱ የተጠራችሁበት ተስፋ ምን እንደሆን፥ ከቅዱሳንም ጋር የሚኖራችሁን የርስት ክብር ባለጠግነት ምንነት እንድታውቁ፥ የልቦናችሁ ዐይኖች እንዲበሩ፤
መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚናገረውን ጆሮ ያለው ይስማ። ድል ለነሣው ከተሰወረ መና እሰጠዋለሁ፤ ነጭ ድንጋይንም እሰጠዋለሁ፤ በድንጋዩም ላይ ከተቀበለው በቀር ማንም የማያውቀው አዲስ ስም ተጽፎአል።