መዝሙር 22:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ችግረኞች ይበላሉ፥ ይጠግቡማል፥ ጌታንም የሚሹት ያመሰግኑታል፥ ልባቸውም ለዘለዓለም ሕያው ይሁን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የምድር ዳርቻዎች ሁሉ ያስታውሳሉ፤ ወደ እግዚአብሔርም ይመለሳሉ፤ የሕዝቦች ነገዶች ሁሉ፣ በፊቱ ይሰግዳሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስከ ምድር ዳርቻ ያሉ ሰዎች ሁሉ አስታውሰው ወደ እግዚአብሔር ይመለሳሉ፤ በዓለም የሚገኙት ሕዝቦች ሁሉ በፊቱ ይሰግዳሉ። |
እርሱም፦ “የያዕቆብን ነገዶች እንድታስነሣ ከእስራኤልም የተረፉትን እንድትመልስ አገልጋዬ እንድትሆን እጅግ ቀላል ነገር ነውና ማዳኔ እስከ ምድር ዳር እንዲደርስ ለአሕዛብ ብርሃን አድርጌ ሰጥቼሃለሁ ይላል።
እንዲህም አሉ “እናንተ ሰዎች! ይህን ስለምን ታደርጋላችሁ? እኛ ደግሞ እንደ እናንተ የምንሰማ ሰዎች ነን፤ ከዚህም ከንቱ ነገር ሰማይንና ምድርን ባሕርንም በእርነርሱም ያለውን ሁሉ ወደ ፈጠረ ወደ ሕያው እግዚአብሔር ትመለሱ ዘንድ ወንጌልን እንሰብካለን።
እነርሱ ራሳቸው ስለ እኛ በእናንተ መካከል ምን ዓይነት አቀባበል ተደርጎልን እንደ ነበር፥ ሕያውም የሆነውን እውነተኛ አምላክ ለማገልገል ከጣዖታት ወደ እግዚአብሔር እንዴት እንደተመለሳችሁ፥