ብዙ ውሾች ከብበውኛልና፥ የክፋተኞች ጉባኤም አገተኝ፥ እጆቼንና እግሮቼን ቸነከሩኝ።
ዐጥንቶቼን ሁሉ አንድ በአንድ መቍጠር እችላለሁ፤ እነርሱም አፍጥጠው ይመለከቱኛል።
አጥንቶቼ ተቈጠሩ፤ ጠላቶቼም አተኲረው እያዩ በማፌዝ ተመለከቱኝ።
ሥጋው እስከማይታይ ድረስ ይሰለስላል፥ ተሸፍኖ የነበረውም አጥንት ይገለጣል።
ፊቱ ከሰዎች ሁሉ ይልቅ፥ መልኩም ከሰዎች ልጆች ይልቅ ተጐሳቁሎአልና ብዙ ሰዎች ስለ አንተ እንደ ተደነቁ፥ እንዲሁ ብዙ አሕዛብን ያስደንቃል፤
በዚያም ተቀምጠው ይጠብቁት ነበር።
ከሕዝቡ እጅግ ብዙ ሰዎችና ደረታቸውን እየመቱ የሚያለቅሱለት ብዙ ሴቶች ተከተሉት።
ሕዝቡም ቆመው ይመለከቱ ነበር። መኰንኖቹም “ሌሎችን አዳነ፤ እርሱ በእግዚአብሔር የተመረጠው ክርስቶስ ከሆነ፥ ራሱን ያድን፤” እያሉ ያፌዙበት ነበር።