ቀን ለቀን ንግግርን ታወጣለች፥ ሌሊትም ለሌሊት እውቀትን ትናገራለች።
ንግግር የለም፤ ቃል የለም፤ ድምፃቸው በጆሮ የሚሰማ አይደለም።
ንግግር ወይም ቃላት የላቸውም፤ ድምፃቸውም አይሰማም፤
መሥዋዕትህን ያስብልህ፤ ቍርባንህንም ያለምልምልህ።
ዐይኖችህን ወደ ሰማይ አንሥተህ፥ ጌታ አምላካችሁ ከሰማይ በታች ላሉት ሕዝቦች ሁሉ የሰጣቸውን፥ ፀሐይንና ጨረቃን ከዋክብትንም፥ የሰማይን ሠራዊት ሁሉ ባያችሁ ጊዜ፥ በመሳት እንዳትሰግዱላቸውና እንዳታመልኳቸው ተጠንቀቁ።