ነፍሴ በውስጤ አለቀችብኝ፥ ልቤም በውስጤ ደነገጠብኝ።
ስለዚህ መንፈሴ በውስጤ ዝላለች፤ ልቤም በውስጤ ደንግጧል።
ከዚህም የተነሣ መንፈሴ በውስጤ ዛለብኝ፤ ልቤም ተስፋ ቈረጠ።
ሰው ከንቱ ነገርን ይመስላል፤ ዘመኑም እንደ ጥላ ያልፋል።
በድሀ አደጉ ላይ ዕጣ ትጣጣላላችሁ፥ ለወዳጆቻችሁም ጉድጓድ ትቈፍራላችሁ።
ባዘነና ልመናውን በጌታ ፊት ባፈሰሰ ጊዜ የችግረኛ ጸሎት።
በዚያን ጊዜ ውኃ ባሰጠመን ነበር፥ በነፍሳችንም ላይ ወራጅ ውኃ ባለፈ ነበር፥
ሮሮዬን በፊቱ አፈስሳለሁ፥ መከራዬንም በፊቱ እናገራለሁ።
መንፈሴ በዛለ ጊዜ መንገዴን አወቅሁ፥ በምሄድባት በዚያች መንገድ ወጥመድን ሰወሩብኝ።
እኔ ብቸኛና የተጨነቅሁ ነኝና ፊትህን ወደ እኔ መልስ ማረኝም።
ልቤ በላዬ ተናወጠብኝ፥ የሞት ድንጋጤም ወደቀብኝ።
አምላክ ሆይ፥ ጩኸቴን ስማ፥ ጸሎቴንም አድምጥ።
በመከራዬ ቀን ጌታን ፈለግሁት፥ እጆቼ በሌሊት በፊቱ ናቸው፥ አላረፍሁምም፥ ነፍሴም መጽናናትን አልቻለችም።
የዱሮውን ዘመን አሰብሁ፥ የጥንቱን ዓመታት አሰብሁ፥
በስቃይ ጣር ውስጥ ሆኖ በብርቱ ይጸልይ ነበር፤ ላቡም ወደ መሬት እንደሚንጠባጠቡ የደም ጠብታዎች ሆኑ።