እኛ ሕያዋን ግን ከአሁን ጊዜ ጀምሮ እስከ ዘለዓለም ጌታን እንባርካለን። ሃሌ ሉያ።
ከአሁን ጀምሮ እስከ ዘላለም፣ እግዚአብሔርን የምንባርክ እኛ ነን። እግዚአብሔር ይመስገን።
እኛ ግን በሕይወት ያለነው ከአሁኑ ጊዜ ጀምሮ እስከ ዘለዓለም እናመሰግነዋለን። እግዚአብሔር ይመስገን!
ከአሁን ጀምሮ እስከ ዘለዓለም ድረስ የጌታ ስም ቡሩክ ይሁን።
በየቀኑ ሁሉ እባርክሃለሁ፥ ስምህንም ለዘለዓለም ዓለምም አመሰግናለሁ።
አፌ የጌታን ምስጋና ይናገራል፥ ሥጋም ሁሉ ለዘለዓለም ዓለም የተቀደሰውን ስሙን ይባርክ።
በሰማይና በምድርም ከምድርም በታች በባሕርም ላይ ያለ ፍጥረት ሁሉ በእነርሱም ውስጥ ያለ ሁሉ “ውዳሴ ገናናነት ክብርም ኃይልም ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው፥ ለበጉም ይሁን፤” ሲሉ ሰማሁ።