የአሕዛብን ርስት ይሰጣቸው ዘንድ ለሕዝቡ የሥራውን ብርታት አሳየ።
ለሕዝቡ የአሕዛብን ርስት በመስጠት፣ የአሠራሩን ብርታት አሳይቷል።
የሕዝቦችን ርስት በመስጠት ታላቅ ኀይሉን ለወገኖቹ አሳይቶአል።
ለዘለዓለም አይታወክም፤ የጻድቅ መታሰቢያ ለዘለዓለም ይኖራል።
ለሙሴ መንገዱን አስታወቀ፥ ለእስራኤል ልጆችም ድንቅ ሥራዎቹን።
ለሰው ልጆች ኃይልህን የመንግሥትህንም ግርማ ክብር ያስታውቁ ዘንድ
ለምነኝ፥ አሕዛብን ለርስትህ የምድርንም ዳርቻ ለግዛትህ እሰጥሃለሁ።
አቤቱ፥ በጆሮአችን ሰማን፥ አባቶቻችንም በዘመናቸው በቀድሞ ዘመን የሠራኸውን ሥራ ነገሩን።
እጅህ አሕዛብን አባረረች፥ እነርሱንም ተከልህ፥ አሕዛብን አስጨንቀህ እነሱን አለመለምክ።
በሰይፋቸው ምድርን አልወረሱም ክንዳቸውም አላዳናቸው፥ ቀኝህና ክንድህ የፊትህም ብርሃን ነው እንጂ፥ ወድደሃቸዋልና።
የሠራዊት አምላክ አቤቱ፥ መልሰን፥ ፊትህንም አብራ፥ እኛም እንድናለን።
ሕዝቡም ጮኹ፥ ካህናቱም ቀንደ መለከቱን ነፉ፤ ሕዝቡም የቀንደ መለከቱን ድምፅ በሰሙ ጊዜ ታላቅ ጩኸት ጮኹ፥ ቅጥሩም ወደቀ፤ ሕዝቡም ሁሉ እያንዳንዱ በቀጥታ አቅንቶ ወደ ከተማይቱ ወጣ፥ ከተማይቱንም ያዝዋት።