አኪጦፌልም ምክሩን እንዳልተከተሉት ባየ ጊዜ፥ አህያውን ጭኖ ቤቱ ወደሚገኝበት ወደ መኖሪያ ከተማው ሄደ፤ ቤቱንም አስተካክሎ በገዛ እጁ ታነቀ፤ ከሞተ በኋላ በአባቱም መቃብር ተቀበረ።
መዝሙር 109:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህ ቅጣት በሚከሱኝና በነፍሴም ላይ ክፉን በሚናገሩ ላይ ከጌታ ዘንድ ይሁን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ለሚወነጅሉኝ ሰዎች፣ በነፍሴም ላይ ክፉ ለሚናገሩ የሚከፍላቸው ይኸው ይሁን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሆይ! ይህን ሁሉ ክፉ ነገር በእኔ ላይ የሚናገሩትን ጠላቶቼን በዚህ ዐይነት ቅጣቸው። |
አኪጦፌልም ምክሩን እንዳልተከተሉት ባየ ጊዜ፥ አህያውን ጭኖ ቤቱ ወደሚገኝበት ወደ መኖሪያ ከተማው ሄደ፤ ቤቱንም አስተካክሎ በገዛ እጁ ታነቀ፤ ከሞተ በኋላ በአባቱም መቃብር ተቀበረ።
ንጉሡም ኢትዮጵያዊውን፥ “ወጣቱ አቤሴሎም ደኅና ነውን?” ሲል ጠየቀው። ኢትዮጵያዊውም፥ “የጌታዬ የንጉሡ ጠላቶችና ሊጐዱህ የሚነሡብህ ሁሉ እንደዚያ ወጣት ይሁኑ” ሲል መለሰ።
ስለዚህ ማንም በእግዚአብሔር መንፈስ ሲናገር “ኢየሱስ የተረገመ ነው፤” የሚል እንደሌለ፥ በመንፈስ ቅዱስም ካልሆነ በቀር “ኢየሱስ ጌታ ነው፤” ሊል ማንም እንደማይችል አስታውቃችኋለሁ።