መዝሙር 107:40 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመኰንኖችም ላይ ውርደትን ዘረገፈ፥ መንገድም በሌለበት በምድረ በዳ አንከራተታቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመኳንንቱም ላይ መናቅን አዘነበባቸው፤ መውጫ መግቢያው በማይታወቅ በረሓ ውስጥም አንከራተታቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ልዑላኑን አዋረደ፤ በምድረ በዳም አሸዋ ውስጥ እንዲንከራተቱ አደረገ። |
ሕዝቤን ባትለቅቅ፥ እነሆ በአንተ ላይ፥ በአገልጋዮችህ ላይ፤ በሕዝብህ ላይ፥ በቤቶችህም ላይ የዝንብ መንጋ እልካለሁ፤ የግብፃውያንም ቤቶች፥ የቆሙባትም ምድር ሁሉ በዝንብ መንጋ ይሞላሉ።
ፈርዖንም ሙሴንና አሮንን ጠርቶ “እንቁራሪቶቹን ከእኔና ከሕዝቤ እንዲያርቅ ወደ ጌታ ጸልዩልኝ፤ ለጌታም እንዲሠዋ ሕዝቡን እለቅቃለሁ” አላቸው።
የነገሥታትን ሥጋና የሻለቃዎችን ሥጋ የብርቱዎችንም ሥጋ የፈረሶችንም በእነርሱም የተቀመጡትን ሥጋ የጌታዎችንና የባርያዎችንም የታናናሾችንና የታላላቆችንም ሁሉ ሥጋ ትበሉ ዘንድ” ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ።
የሔቤር ሚስት ያዔል ግን ሲሣራ ደክሞ፥ ከባድ እንቅልፍም ወስዶት ሳለ፥ የድንኳን ካስማና መዶሻ ይዛ በቀስታ ወደ እርሱ ቀረበች፤ ከዚያም ካስማውን በመዶሻ ጆሮ ግንዱ ላይ መትታ ከመሬት ጋር ሰፋችው፤ እርሱም ሞተ።
ነገር ግን ታቦቱን ወደዚያ ከወሰዱትም በኋላ የጌታ እጅ በከተማዪቱ ላይ ሆነ፤ ታላቅ መሸበርም አመጣባቸው፤ ሕፃን ሽማግሌ ሳይል ሕዝቡን በእባጭ መቅሠፍት መታ።
እነርሱም፥ “የምንልከው የበደል መሥዋዕት ምን መሆን አለበት?” ሲሉ ጠየቁ። እነርሱም እንዲህ ሲሉ መለሱ፤ “እናንተንም ሆነ አለቆቻችሁን የመታው መቅሠፍት አንድ ዓይነት በመሆኑ፥ በፍልስጥኤማውያን ገዥዎች ቍጥር አምስት የወርቅ ዕባጮችና አምስት የወርቅ ዐይጦች ላኩ።