ምድረ በዳን ወደ ውኃ ማጠራቀምያ፥ ደረቁንም ምድር ወደ ውኃ ምንጭነት ቀየረ።
ምድረ በዳውን ወደ ውሃ መከማቻ፣ ደረቁንም ምድር ወደ ውሃ ምንጭ ቀየረ።
እንደገናም በበረሓው ብዙ ኲሬዎች እንዲኖሩ፥ በደረቁም ምድር ብዙ ምንጮች እንዲገኙ አደረገ።
ሣሩንም እንዲያበቅል፥ ማንም በሌለባት ምድር ላይ፥ ሰውም በሌለባት ምድረ በዳ ላይ ዝናብ እንዲዘንብ፥ ለፈሳሹ ውኃ መተላለፊያውን፥ ወይም ለሚያንጐደጉድ መብረቅ መንገድን ያበጀ ማን ነው?
ዐለቱን ወደ ውኃ መቆሚያ፥ ድንጋዩንም ወደ ውኃ ምንጭ ይለውጣል።
ውኃን ከዓለት አወጣ፥ ውኃንም እንደ ወንዞች አፈሰሰ።